መቸም ድህነት እንጂ ስልጣን ከአንዱ ወደሌላው በሰላም በማይተላለፍባት ሀገር ኢትዮጵያ ላለን ሰዎች፣ ሌሎች የሚያደርጉት ምርጫ (የምክር ቤት ይሁን የመራሂ መንግስት) እና የስልጣን ሽግግር ሁሌም እንዳማለለን፣ አፍ እንዳስከፈተን አለ፡፡ ሁነቱ ዕንቆቅልሽ ለሆነበት፣ እንደሌሎች ማድረግ ላልተቻለው ሀበሽ በርግጥ ትንግርት መምሰሉ ይገባው እንደሁይ አይበዛበትም፡፡ ሺህ አመታትን በጠንካራ መንግስትነት፣ ቅኝ ሳትገዛ የኖረች ሀገር ኢትዮጵያ፣ በፈጣሪ ቸርነት ይሁን ቸርነቱ ከኛ በላይ በጠቀማቸው መሪዎቿ፣ ሕዝቦቿ ምርጫ ማለት ምንና እንዴት እንደሆነ ሳይገነዘቡባት፣ ሳንገነዘብባት ዘበን በዘበን ላይ እየተደራረበ አለፈ፣ ነጎደ፣ እየነጎደም ነው፡፡
የሃያኛው ክፍለ ዘመን ካፈራቸው የሽምቅ ውጊያ አዋቂዎች ተርታ ግንባር ቀደሙን ቦታ ይይዛሉ የተባለላቸው የታንሺር ሸለቆው ጀግና፣ 200, 000 ሰራዊት አስከትሎ ሃገራቸው አፍጋኒስታንን የወረረውን የሶቪየት ጦር ከወንዛቸው ልጆች ጋር በመሰለፍ በተነገረለት የጦር ጥበባቸው ስለሃገር ክብር መመለስ ሲፋለሙ፣ ወራሪውን ጦር መቆሚያ መቀመጫ በመንሳት በ1989 ድል ሲነሱት ያስተዋለ እኒሕ ጀግና…
እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ19ኛው መቶ ጅማሬ አንስቶ በስፋት ይብላላ ነበር የተባለለትና እስራኤላዊያንን ወደ “ተስፋይቱ ምድር” የማስገባት፣ ሃገርም የመመስረትን ህልም ውል ያስያዙ፣ አባት የሆኑለት ሰው ቴዎዶር ኸርዝል መሆናቸው አለም የሚያውቀው የታሪክ ድርሳናት መዝግበው ያኖሩት ሐቅ ነው፡፡
እነዚህ “ጌታ የመረጠን” ያሉ የአለማችን ህዝቦች ምንም እንኳ ከአህዛብ በተለየ የሰማያዊው ፈጣሪ በረከት…
“እንደኔ እንደኔ ከሁሉም በላይ የቁርዓን አስደናቂነቱ የተራማጅነት ይዘቱ ነው: የሌላ ዕምነት ተከታይ እንደመሆኔ ይህን ፅሁፍ በታላቅ ትህትና ፅፈዋለሁ፡፡ ከዕምነቱ ውጭ እንዳለ ሰው ሳየው ቁርዓን የተሃድሶ መፅሃፍነቱ ግርምት ይፈጥርብኛል…”
የዕምነት መሰረታቸውን በኣንድ ፈጣሪ ላይ መስርተዋል ለሚባልላቸውና የነቢዩ ኢብራሂም (የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይውረድ) ልጆች ለሚከተሉዋቸው ሶስቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች- የአይሁድ እምነት፣ ክርስትና፣ እና እስልምና (ሞኖቴኢስቲክ ኤብረሃሚክ ሪሊጅንዝ) ሁሉ የዕምነታቸው መነሻና መድረሻ ያህል የምትቆጠረው ትንሽዬ ከተማ አል ቁድስ (እየሩሳሌም)በርግጥ ለሁሉም ቅድስት ከተማቸው መሆንዋ አስረጂ የማይሻ እውነት ነው፡፡
